የፀጥታው ምክር ቤት በማሊ ላይ ማእቀብ ጣለ

ጳጉሜ 1፤2009

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሰላም ጥረትን እያስተጓጉሉ ነው ባላቸው የማሊ ግለሰቦች ላይ ማእቀብ መጣሉን አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዳይመጣ እንዲሁም አገሪቱ እንዳትረጋጋ አስተጓጉለዋል በሚል በለያቸው ግለሰቦች ላይ ነው የጉዞና ሀብት እገዳ ውሳኔ  ያስተላለፈው፡፡

አስራ አምስት አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ባሳለፈው ውሳኔ ለመነሻ ማእቀቡ ለ13 ወራት እንዲቆይ ወስኗል፡፡

እኤአ 2015 በማሊ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የፀጥታው ምክር ቤት ስምምነቱን በማያከብሩ ላይ እርምጃውን ወስዷል፡፡

ማሊ የባለፈው ወር የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ለነበረችው ግብፅ በአማፂ ቡድኑ ላይ ማእቀብ እንዲጣል ጥያቄ አቅርባለች፡፡   

ምንጭ፡- የተባበሩት መንግስታት