የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጦርነትን እየመረጠ ነው

ነሃሴ 30፤2009

የሃይድሮጅን ቦንብ ሙከራ በማድረግ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጦርነትን እየመረጠ ነው በማለት በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምበሳደር ተናገሩ᎓᎓

አምባሳደራ ኒኪ ሃለይ የጸጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በኒዮርክ በተካሄደበት ወቅት እንደተናገሩት አሜሪካ ጦርነት አትፈልግም ትእግስቷ ግን ገደብ አለው ብለዋል᎓᎓

አሜሪካ የተባበሩት መንድስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለውን ማእቀብ ለማጠንከር አዲስ ውይይት እንዲደረግ እንደምትፈልግ ተናግረዋል᎓᎓

በተለይም ደግሞ አሜሪካ አሁን በሀገሪቱ ላይ እንዲጣል የምትፈልገው ማዕቀብ ነዳጅ ወደ ሀገሯ እንዳታስገባ የሚከልክለውን ሊያካትት ይችላል እየተባለ ነው፡፡

የሩሲያ ፕሬዚደንት ብለድሚር ፑቲን ግን ማእቀቡ የማይረባና ጥቅም የሌለው በማለት አጣጥለውታል᎓᎓

የሰሜን ኮሪያ ዋነኛ አጋር የሆነችው ቻይና ደግሞ አዲስ ውይይት እንዲደረግና ሲውዘርላንድ አሸማጋይ እንድትሆን አዲስ ሃሳብ አቅርባለች᎓᎓