የኬንያ ዳግም ምርጫ ቀን ተቆረጠለት

ነሀሴ 30፤2009

በኬንያ ተካሂዶ የነበረውና በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ የተደረገው ምርጫ ጥቅምት 7 በድጋሚ እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡

በድጋሚ በሚደረገው ምርጫ ላይ ለውድድር የሚቀርቡት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እና ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ እንደሚሆኑ የምርጫ ቦርዱ አስታውቋል፡፡

ባለፈው ወር በተደረገው ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ አሸናፊ እንደሆኑ መገለፁ ይታወሳል፤ ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስም ተሰሚነት አግኝቶ ምርጫው ውድቅ እንዲደረግ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለተቃዋሚ በመፍረድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲደገም ያደረገ በመሆኑ በአፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በኬንያ ፍርድ ቤት የተወሰነውን አነጋጋሪ ውሳኔ የአፍሪካ ህብረቱ ሊቀመንበር አልፋ ኮንዴ አፍሪካን የሚያኮራ ውሳኔ ነው ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡

አርብ እለት ምርጫው እንዲደገም 6 አባላት የተሳተፉበት የጠቅላይ ፍርድቤት የዳኞች ቡድን 4 ለ2 በሆነ የድምጽ አብላጫ ወስነው ነበር፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ሲጂቲኤን