ኬንያውያን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በፀጋ እንዲቀበሉ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

ነሐሴ 25፣2009

ኬንያውያን በተቃዋሚ ፓርቲው ኤን ኤ ኤስ ኤ ባቀረበው የተቃውሞ ፊርማ አቤቱታ ላይ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ በፀጋ እንዲቀበሉ የአፍሪካ ህብረት አሳስቧል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ አርብ እለት ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲው ዘንድሮ በኬንያ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ ነው ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የተቃውሞ ፊርማውን ያሰባሰበው፡፡

የአፍሪካ ህብረት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚዎቹን ጉዳይ ተቀብሎ ለመመልከት ፍቃደኛ በመሆኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡  

የህብረቱ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በሁለቱም ወገን ያሉ አካላት በምርጫው ውጤት የተነሳ የተፈጠረውን ቅራኔ ለመፍታት ከፀብ ይልቅ ሰላማዊውንና ህጋዊ የሆነውን መንገድ አሟጠው እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ምክር ቤቱ አክሎም ከድህረ-ምርጫው ወዲህ የኬንያን ጉዳይ በጥብቅ ለመከታተል ከስምምነት መደረሱን አስታውቋል፡፡ 

ኬኒያውያን ምርጫውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ አሸናፊ መሆናቸው  ከተገለፀ በኃላ ላሳዩት ትእግስትና መረጋጋትም ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡ 

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን