ደቡብ ኮሪያ የሳምሰንግ ኩባንያን ወራሽ በሙስና ምክንያት በ5 ዓመት እስር ቀጣች

ነሐሴ 19፣2009

ደቡብ ኮሪያ የሳምሰንጉ ኩባንያ ወራሽ ሊ ጃኢ ዮንግን  በሙስና ምክንያት በአምስት ዓመት እስራት ቀጣች፡፡

የደቡብ ኮሪያው ፍርድ ቤት ዛሬ ባሳለፈው የእስር ቅጣቱን ውሳኔ  ቢሊዬነሩና የኩባንያው ወራሽ ሊ ጃኢ ዮንግ ከስልጣናቸው ከተወገዱት  የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር በሙስና እጃቸው አለበት በሚል ሲካሄድባቸው የነበረውን ምርመራ በማስረጃ በማረጋገጡ ነው፡፡

ባለሀብቱ በእንዲህ አይነት ቅሌት ወህኒ መግባታቸው በአገሪቱ ያሉ ኩባንያዎች እየፈፀሙት ላለው ደባና ለህዝብ ቁጣ የተሰጠ መቀጣጫ ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ይሁንጂ ባለሀብቱ ሊ የቀረበባቸውን ክስ ሁሉ ውድቅ ቢያደርጉም በሌሎች ተጨማሪ ክሶች እስከ 12 ዓመት  በእስር ህይወታቸውን ሊመሩ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

ይሁንጂ የባለ ሀብቱ ጠበቃ ፍርዱ አግባብነት የለውም በሚል አቤት እንደሚሉ ተናግረዋል፡፡

በአለም የአሌክትሮኒክስ ገበያ ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለት የሳምሰንግ ዋና ኃላፊ  ጭምር የነበሩት ባለሀብቱ፣ ከባለፈው የካቲት ጀምሮ  በጉቦ፣የህዝብ ሀብት ምዝበራና በውጭ አገራት ያላቸውን ሀብት መሰወርን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀል ነክ ጉዳች ተጠርጥረው ነበር ለእስር የተዳረጉት፡፡

በተለይም ለቀድሞዋ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፓርክ ገዩን ሄይ የቅርብ ወዳጃ ለሚመራ አንድ የበጎ አድራት ድርጅት 36 ሚሊዮን ዶላር ስጦታ በመስጠት በእጅ አዙር ፖሊቲካዊ ውለታ አግኝተዋል የሚለው ትልቁ ክስ ነው፡፡በዚህም ግለሰቡ በልዩ ሁኔታ በሳምሰንግ ላይ የተለየ የበላይነት እንዲኖር በር ተከፍቶላቸዋል የሚለው ክስ ለፕሬዝዳንቷም ጭምር ተርፎ  ከስልጣናቸው ወርደው ለህግ እንዲቀርቡ ያደረገ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል፡፡

በሳምሰንጉ ወራሽ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የኩባንያው ድርሻ በአክስዮን ገበያ የ1 በመቶ ማሽቆልቆል ታይቶበታል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ