ቻይናና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳች ላይ መከሩ

ነሐሴ 13፣2009

ቻይናና ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ግንኙነታውን በሚያጠናክሩ ጉዳች ላይ መከሩ ፡፡

የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ከፍተኛ ኃላፊዎች  በቻይና ቤጂንግ የመከሩት በትላንትናው ዕለት ነው፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ሳሙራ ዩኒስና የቻይናው ማዕከላዊ ወታደራዊ ምክትል ሊቀ መንበር ፋን ቻንግሎንግ ናቸው በሁለቱ አገራት ወታራዊ መስክ ትብብር ዙሪያ የመከሩት፡፡

ፋን ቻንግ ሎንግ ለሽንዋ እንደተናገሩት  ሁለቱ አገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ ፖለቲካዊ ትብብራቸው ውጤማ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ቻይናም ከኢትዮጵያ ጋር በወታራዊ መስኩ የጠነከረ ትብብር በማድረግ ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ ዘርፍ ስትራቴጂያዊ አጋሯ ሆና እንድትቀጥል ፍላጎቷ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ