ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሩዋ|ንዳ ኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ

ነሃሴ 12፤2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ጉብኝታቸው መጠናቀቅ በኋላ ዛሬ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው የሀገሪቱ ኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በዓለ ሲመት ላይ ታድመዋል፡፡

የሩዋንዳው ኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ የበዓለ ሲመት ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ነው የተከናወነው፡፡

ፓል ካጋሜ ባለፈው ወር መጨረሻ በሀገሪቱ በተካሔደ ኘሬዝዳንታዊ ምርጫ ነበር ለ3ኛ ጊዜ የተመረጡት፡፡

የመራጩን ህዝብ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ያሸነፉት ፓል ካጋሜ ለቀጣዮቹ 7 ዓመታት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር በመሆን ያገለግላሉ፡፡