የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በምጣኔ ሃብት ውህደት ድህነትን መቀነስ አለባቸው- ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ደሳለኝ

ነሃሴ 12፤2009

የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ቀጠናዊ የምጣኔ ሃብት ውህደት በመፍጠር ዜጐቻቸውን ከድህነት ለማላቀቅ እንዲሠሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ካርቱም ከተለየዩ አካላት በተገኙበት መድረክ ላይ ስለቀጠናው ነባራዊ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡