በቡኖ በደሌ ዞን በመኸሩ ከ9ዐ ሺ ሄክታር በላይ መሬት በሰብል መሸፈኑ ተገለጸ

ነሃሴ 12፤2009

በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በተያዘው መኸር ከ9ዐ ሺ ሄክታር በላይ መሬት በሰብል መሸፈኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ምርታማነትን ለማሳደግም 5 ሺህ ኩንታል የምርጥ ዘርና ከ65ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፡፡