በአሜሪካ አየር ጥቃት ሰባት የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

ነሃሴ 12፤2009

አሜሪካ በሶማሊያ በካሄደችው የአየር ድብደባ 7 የአልሻባብ ታጣቂዎች መግደሏን አስታወቀች፡፡

በአፍሪካ የአሜሪካ ጠር እዝ እንደገለጸው ሰባቱ የአልሻባብ ታጣቂዎች የተገደሉት በደቡብ ምዕራብ ሞቃዲሾ ሶስት የአሜሪካ የጦር አውፕላኖች በካሄዱት ድብደባ ነው፡፡

 የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች  ከሶማሊያ የጦር ኃይል ጋር በመተባበር ከሞቃዲሾ 320 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የአገሪቱ ደቡብ ምእራብ  አካባቢ ድብደባውን ማካሄዳቸው ተገልጿል፡፡

 ምንጭ -ሮይተርስ