በኡጋንዳ የተጠለሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች 1 ሚሊዮን ደረሰ

ነሃሴ 11-2009

ኡጋንዳ  ወደ ሀገሯ የተሰደዱትን አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን  ስደተኞችን ለማስተናገድ እየታገለች መምጣቷን የተባሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅት እንደገለፀው በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች  በሀገራቸው የተከሰተውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመሸሽ  ወደ ኡጋንዳ የተሰደዱት  አንድ ሚሊዮን በመድረሱ አገሪቱ ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡

እ.አ.አ.በ1994 በሩዋንዳ ከተከሰተው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ቀጥሎ የደቡብ ሱዳኑ የእርስ በርስ ግጭት ትልቁ የአፍሪካ ስደተኞች ችግር መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

ድርጅቱም ለስደተኞቹ በየጊዜ እየለመነ የሚያደርሰው የሰብዓዊ እርዳታ ከሚያኘው አንፃር አስቸጋሪ እንደሆነበት አመልክቷል፡፡

ኡጋንዳ ከገቡት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መካከል 85 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ህፃናት ናቸው ተብሏል፡፡

ከኡጋንዳ በተጨማሪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናዊያን የእርስ በርስ ግጭቱን በሸሽ ወደ ኢትዮጵያም ገብተው ተጠልለው ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፡‑  ሲጂቲኤን