ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባው ምርት 5ዐ በመቶውን በሱዳን ወደብ በኩል ልታደርግ ነው

ነሐሴ11፣2009

ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባው ምርት 5ዐ በመቶውን በሱዳን ወደብ በኩል የማስገባት ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡

ይህንን እውን ለማድረግ ራሱን የቻለ ተርሚናል እንዲኖራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

 ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባቸው ምርቶች  ግምሽ ያህሉን በሱዳን በኩል የማስገባት ፍላጎት እንዳት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት በሁለቱ አገራት ሁለንተናዊ ትብብር ዙሪያ  ከፕሬዝዳንት አልበሽር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውይይቱ በኋላ  እንደገለጹት አሁን ኢትዮጵያ የምትጠቀመው የጅቡቲ ወደብ ለአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ሩቅ በመሆኑ  ለተጨማሪ የትራንስፖርትወጪ እየዳረጋት ነው።

ኢትዮጵያ 50 በመቶ የገቢ ምርቷን በሱዳን በኩል የማስገባት  እቅዷን ለማሳካት በሁለቱ ሀገራት በኩል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ሀገራቱ በሁሉም ዘርፍ ያላቸውን ትብብር  አጠናክረው ለማስቀጠል  ለመሰረተ ልማት ስራዎች ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡‑ ኢዜአ