በቀጣይ ዓመት የነዳጅ ምርት ፍላጎት ጭማሪ እንደሚያሳይ ተገለጸ

ነሐሴ 05፣2009

የነዳጅ ላኪዎች ህብረት /ኦፔክ/ በቀጣይ ዓመት ያልተጣራ የነዳጅ ምርት ፍላጎት በገበያ ላይ ጭማሪ እንደሚያሳይ  አስታወቀ፡፡

እንደ ድርጅቱ ትንበያ ለሚቀጥለው አመት በዓለም ላይ ባለፈው አመት ከነበረው ተጨማሪ 220 ሺህ በርሚል ነዳጅ ፍላጎት ይኖራል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ ዓመት ከ32 እስከ 42 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ በቀን ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡

የኦፔክ አባል ሀገራት ያደረጉት የነዳጅ ምርት ቅነሳ  አቅርቦቱን ተመጣጣኝ እያደረገ መሆኑንም ዘገባው ያትታል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሚቀርበው የነዳጅ አቅርቦት ከፍላጎት በላይ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡