ደቡብ ሱዳን የመንገድና የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትገነባ ነው

ነሀሴ 4 ፤2009

ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር አካባቢ የመንገድ፤ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርና የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል ግንባታዎችን ለማካሄድ ማቀዷን አስታወቀች፡፡

ሀገሪቱ ይህን እቅዷን ይፋ ያደረገቺው ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘውንና የአማጺያኑ ጠንካራ ይዞታ የነበረቺውን የፓጋግ ከተማን የመንግስት ጦር ነጻ ካወጣ በኋላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጄምስ ሞርጋን ለሺንዋ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በዚህ አመት መጀመሪያ አካባቢ የኢኮኖሚ መግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ቢያቅዱም መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የድንበር አካባቢ በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር ስለነበር ነው፡፡

ሀገሪቱ ይህንን ፕሮጀክት እውን ማድረግ መፈለጓ በአየር ተገድቦ የቆየውን የመጓጓዣ ዘዴን በምድርም ለማድረግ ሲሆን የተጣራ የነዳጅ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመላክም እንደሚረዳት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ