የኢራኑ ፕሬዝዳን ሴት ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ሾሙ

ነሐሴ 03፤2009

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮውሀኒ ሶስት ሴት ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ሾሙ።

ፕሬዝዳንቱ ሴቶቹን የሾሙት በካቢኔያቸው ሴቶችን አላካተቱም በማለት ትችት እየተሰነዘረባቸው ባለበት ወቅት ነው ተብሏል።

ተሾሚዎቹ  ማሱሜህ ኢብቴካር የቤተሰብ እና ሴቶች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ላያ ጆኔይዲ የህግ ጉዳዮች  ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ሻሂንዶክት ሞውላቬርዲ የዜጎች መብት ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው።

ፕሬዝዳንቱ  12 ምክትሎች ያሏቸው ሲሆኑ  የፕሬዝዳንቱ ተጠሪ  ተቋማትን ይመራሉ ተብሏል።

በፓርላማ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው ካቢኔው ከሴቶች በተጨማሪ ከአገሪቱ 10 ከመቶ የሚሆኑት ሱኒዎች አባላትም አነስተኛ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢራን እስላማዊ አብዮት ከተካሄደ ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1979 ወዲህ አንድ ሴት ብቻ ናቸው የካቢኔ አባል የሆኑት።

በአገሪቱ ታሪክ ብቸኛዋ ሴት የካቢኔ አባል በመሆን ያገለገሉት ማርዚክ ዳስትጄርዲ ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2009-13 የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስትር በመሆን ማገልገላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።