የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮችን የግብር መክፈያ ቀን ተራዘመ

ነሐሴ 01፤2009

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በአዲስ አበባ ያሉ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችን የግብር መክፈያ ቀን እስከ ነሀሴ 1ዐ/2009 ዓ.ም  ማራዘሙን አስታውቋል፡፡

ቀኑን ማራዘም ያስፈለገው ከቀን ገቢ ግመታ ቅሬታ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በቆየው ጫና ምክንያት መሆኑን በባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገልጿል፡፡

በከተማዋ ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች እስካሁን 8ዐ በመቶዎቹ ግብራቸውን ከፍለዋል ብሏል ጽሕፈት ቤቱ፡፡

እስካሁን ግብራቸውን ያልከፈሉም በቀሪ ቀናት እንዲከፍሉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡