አዲሱ አደረጃጀት የደንበኞችን አገልግሎት ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው አየር መንገዱ ገለጸ

ሐምሌ 29፤2009

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞችን አገልግሎት ለማሻሻል በቅርቡ ያጸደቀው አዲስ አደረጃጀት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገለጸ።

አዲስ አደረጃጀቱም የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት፣ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት፣የጭነትና የሎጀስቲክስ ማዕከል፣ የአቢየሽን አካዳሚ፣የኢትዮጵያ የበረራ ምግብ ማደራጃ አገልግሎት፣የኢትዮጵያ የጥገና አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎትን በማጣመር ግዙፍ የአቪየሽን ሕብረት ለማቋቋም ያለመ ነው፡፡

የጥምረቱ መቋቋም ለሀገሪቱ የሚኖረው ፋይዳ አስመልክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማረያምን በኢቢሲ ስቲድዮ ተገኝተውማብራሪያ ሰጥተዋል።