ኢትዮጵያ አግባብነት ያለው የእናት ጡት ምገባ መስፈርትን አላሟላችም፡- የጤና ጥበቃ ሚ/ር

ሐምሌ 28፣2009

ኢትዮጵያ የአለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን የ60 በመቶ አግባብነት ያለው እናት  የጡት ምግባ መስፈርትን አለሟሟላቷን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ቢራራ መለሰ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በመደበኛነት ከ90 ከመቶ የሚሆኑ እናቶች ለህጻናትን ጡት የሚያጠቡ ቢሆንም አለም አቀፍ ደረጃውም አልደረሰም፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2016 አግባብነት ባለው የጡት ምግባዋ 58 ከመቶ ላይ መድረሷን ግን አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ አግባብነት ያለው የጡት ማጥባትን በተፈለገው መልኩ እንዳታከናውን በገጠሩ አካባቢ በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ከተለያዩ ምግቦች ጋር መመገብና በከተማው አካባቢ ደግሞ የዘመናዊ ህይወት ዘይቤ እየተስፋፋ መምጣቱ ዋንኛ ምክንያት መሆናቸውን አቶ ቢራራ መለሰ ለኢቢሲ በስልክ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታትም በሁሉም ክልሎች የግንዛቤ ማስጨበጭ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታትም በአገር አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ ሊያሳድጉ የሚችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ስድስት ወርና ከዚያ በላይ አግባብነት ያለው ጡት ለህፃናት የመገቡ እናቶች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ እየተደረገም  ይገኛል ብለዋል፡፡

ህፃናት ከእናት ጡት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ፤ እድገታቸውና ጤንነታቸው የተስተካከለ እንዲሆን እንዲሁም ደግሞ እንገር የሚባለው ደግሞ ልክ እንደ ክትባት በሽታን ለመከላከል እንደሚረዳ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለህጻናት የተቀነባበረ ወተትና ሌሎች ምግቦችን ቀላቅሎም ሆነ ያለጊዜው መመገብ በህጻናት የወደፊት ህይወት ላይ የተለያዩ የጤንነት ተጽዕኖዎችን ሊያመጣ እንደሚችል ተብሯርቷል፡፡

አየለም ጤና ድርጅት የ193 ሀገራትን ባወጣው መረጃ መሰረት እድሜያቸው ከስድስት በታች የሆኑ ህጻናት መካከል 40 ከመቶው ብቻ የሚሆኑት ብቻ አግባብነት ያለው የጡት ምግባ አግኝተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ 23 ሀገራት በአለም ጤና ድርጅት የተቀመጠውን መስፈርት ያሟሉ ሲሆን ከአፍሪካ ደግሞ ቡሩንዲ፤ ኬፕቨርዴ ኤርትራ፤ ኬንያ፤ ሌሴቶ፤ ማላዊ፤ ርዋንዳ፤ ዩጋንዳና ዛምቢያ ይገኙበታል፡፡

የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት በአለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ሪፖርተር  ፡‑ ዲባባ  ቡራዩ