ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የኤች አይ ቪ ስርጭት ያለባት አገር መሆኗ ተገለጸ

ሐምሌ 25፣2009

ደቡብ አፍሪካ በዓለም ላይ ከፍተኛ የኤች አይ ቪ ስርጭት መጠን እንዳላት የአገሪቱ ስታስቲክስ ኤጄንሲ አመለከተ።

አገሪቱ 12.6 በመቶ የኤች አይ ቪ ስርጭት በመያዝ ከአለም ቀዳሚውን ስፍራ መያዟ የደቡብ አፍሪካ ስተስቲክስ ኤጄንሲ ገልጿል።

የኤጀንሲው መረጃ እንዳመለከተው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2017 7.6 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝቧ በደሙ የኤች አይ ቪ ቫይረስ እንደነበረው ተመልክቷል።

በአገሪቱ ዕድሚያቸው ከ15-49 ክልል ያሉ ዜጎች 18 በመቶው ያህሉ ኤች አይ ቪ በደማቸው እንደምገኝም የአገሪቱ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አመልክቷል።

አገሪቱ ከ3.4 በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ የኤች አይ ቪ ህክምና ፕሮግራም በመስጠትም ከአለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

በደቡብ አፍሪካ ከኤች አይ ቪ ጋር የተያያዙ የጤና ፕሮግራሞች መስፋፋት እንደ ኤች አይ ቪና ቲቢ በመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች የሚከሰት ሞትን እንዲቀንስ ማድረጉንም ተገልጿል።

የአገሪቱ መንግስት የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመከላከል 90-90-90 የሚባል ፕላን ይፋ አድርጋል።

ፕላኑ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2020 በደማቸው ኤች አይቪ ቫይረስ የሚገኝባቸው 90 ከመቶው ዜጎቿ የቫይረሱን ደረጃ ያውቃሉ፤ በተመሳሳይ አመት የኤች አይ ቪ ህክምና ከተደረገላቸው 90 በመቶዎቹ የኤች አይ ቪ ህክምና ያገኛሉ፤ የኤች አይ ቪ መድሀኒት ከሚወስዱ ሰዎች 90 በመቶዎቹ ደግሞ የኤች አይ ቪ ቫይረስ መከላከያ ይወስዳሉ ተብሏል።

ምንጭ፤ ሲጂቲኤን