የጉበት በሽታን ለማጥፋት ትኩረት እንዲሰጥ የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ

ሐምሌ 21፣2009

የዓለም አገራት የጉበት በሽታን ለማጥፋት ቃል የገቧቸውን እርምጃዎች  ወደ ተግባር እንዲቀይሩ የዓለም የጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡

ድርጅቱ ዛሬ በመላው ዓለም ታስቦ የሚውለውን  የጉበት በሽታን አስመልክቶ ነው ለአገራቱ የተግባር እርምጃውን ጥሪ ያቀረበው፡፡

እንደ ድርጅቱ መረጃ እ.አ.አ በ2015 የጉበት በሽታ 1.3 ሚሊዮን ዜጎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡ይህም በሳምባ ምች ከሚሞቱት የሚቀራረብ ሲሆን በኤች አይ ቪ ቫይረስ ከሚሞተው ሰው ቁጥር ደግሞ ይልቃል ብሏል የአለም ጤ ድርጅት፡፡

ከ325 ሚሊዮን ዜጎች በላይ ደግሞ ከበሽታ ጋር ይኖራሉ ያለው ድርጅቱ፣ ከዚህ ውስጥ  በገዳይነታቸው የሚታወቁት  ሄፓታተስ "ቢ" እና "ሲ" የተሰኙት የጉበት ቫይረስ ዓይነቶች ናቸው፡፡

አብዛኛዎቹ ሀገራት የጉበት በሽታ ለማጥፋት እቅድ ያወጡ ቢሆንም ወደ ተግባር መግባት ግን ተስኗቸዋል  ብሏል ድርጅቱ፡፡

በመሆኑም ሀገራቱ በሽታውን ለማጥፋት ቁርጠኛ ሆነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እ.አ.አ በ2015 በበሽታው / በሄፒታይተስ ሲ/ ከተያዙ 71 ሚሊዮን ሰዎች መካከል በሶስት ወር ውስጥ ታክመው መዳን እየቻሉ ወደ ስር ወደ ሰደደው የጉበት በሽታ የሚሸጋገሩት፡፡ከዚህ ውስጥ 7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ህክምና ማግኘታቸውን የድርጅቱ ዘገባ ያመለከተው፡፡

በቫይረስ የሚተላለፈው የጉበት  በሽታ ቀድሞ ከታወቀ በህክምና እንዲድንና ወደ ሌሎች ሳይተላለፍ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ የሚቻል ነው፡፡

ምንጭ፡-ሽንዋ