በአለም አቀፍ ደረጃ በትንባሆ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ የአለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ

ሐምሌ  13፣2009

በሲጋራ ጦስ የሚመጣን ሞት ለመቀነስ በአለም አቀፍ ደረጃ በትንባሆ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር  መደረግ  እንዳለበት  የአለም ጤና ድርጅት አሳሰበ ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በትንባሆ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በአምስት  እጅ ከፍ ቢልም አሁንም ድርጅቱ ተጨማሪ የተጠናከሩ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተለይም አገራት በትንባሆ ምክንያት የሚጠፋን ህይወት መታደግ የሚያስችል ፖሊሲ በመቅረፅ ጭምር ተጨባጭ እርምጃዎችን  እንዲወስዱ    ኢትዮጵያዊዩ የድርጅቱ  ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አሳስበዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ትላንት በትምባሆ ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር የተመለከተ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡የአለማችን  4.7 ቢሊዮን ወይም 63 በመቶ ያህል  ህዝብ  ቢያንስ አንድ ዓይነት የትንባሆ መቆጣጠሪያ ዘንድ በሚተገበርበት መርሆ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይኸው ቁጥር ከ10 አመት በፊት  የአለማችን 15 በመቶ ህዝብ ብቻ ነበር የትንባሆ ቁጥጥር ተደራሽ በሚሆንበት አካባቢ የሚኖረው ፡፡

ትምባሆ  በየአመቱ  ለ7 ሚሊዮን ሰዎች ሞት መንስኤ ከመሆኑ አንፃር ሊከላከሉት የሚቻል ጉዳት ሆኖ እያለ ቸል መባል እንደማይገባ  ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

እንደ ሪፖርቱ መረጃ ከሆነ በትምባሆ ምክንያት በሚደርስ  ሞትና  ህመም አለማችን የ1.4 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ይደርስባታል፡፡

ምንጭ፡ ‑ ሽንዋ