ሁለት እጆቹን በንቅለ ተከላ ያገኘው ህፃን ነገር…

ሃምሌ 12፤2009

በአሜሪካ ገና በሁለት ዓመቱ ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት ሁለት እጆቹን ያጣው ህፃን ከ6 ዓመታት በኋላ በንቅል ተከላ ዳግም እጆቹን አግኝቷል ይለናል የዘ ቴሌግራፍ ድረ- ገፅ፡፡

ይህ አሜሪካዊ ህፃን ጥንድ እጆቹን በንቅለ ተከላ በማግኘትም የዓለማችን የመጀመሪያው ህፃን ሆኗል፡፡

ዚዮን የተባለው ይህ ህጻን የአሜሪካን ቤዝ ቦል የመጫወት ህልም ቢኖረውም እጆቹ ላለፉት 6 ዓመታት አብረውት ባለመኖራቸው ህልም አልባ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን አሁን የተደረገለት ንቅል ተከላ  ህልሙን በደመቀ ተሰፋ መመለሱን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ዚዮን ከንቅለ ተከላው 18 ወራት በኋላ በእጆቹ ራሱን መመገብ እና ማልበስ ችሏል ይላል ዘገባው፡፡

በመሆኑም የዚዮን ህክምና ስኬት ለህክምናው ዘርፍ አዲስ ማበረታቻ ሰጥቷልም ተብሏል ፡፡

ለንቅለ ተከላው የዋሉት እጆች የራሱ ይሁኑ ከሌላ ሰው የተወሰዱ ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡

ምንጭ፡ ዘ ቴሌግራፍ