በኢትዮጵያ ሴቶች ራሳቸው በክርናቸው የሚያደርጉት አዲስ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ተግባር ላይ ሊውል ነው

ሐምሌ 08፣2009

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚውል አዲስ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ በ2ዐ1ዐ ተግባር ላይ እንደሚያውል አስታወቀ፡፡

ለዚህም የብሪታንያ መንግስት የ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የብሪታንያ የአለም አቀፍ የልማት ድርጅት ተወካይ ጆ ኒየር እንዳሉት በድጋፍ ስነስርዓቱ  ወቅት እንዳትሉት እ.ኤ.አ ከ1990  እሰከ 2016 ባሉት ዓመታት የኢትዮጵያ የቤተሰብ ምጣኔ አግልግሎት ከ3 በመቶ ወደ 36 በመቶ ማደጉን መልካም ጅምር ቢሆንም በተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብሪታንያ ድጋፍ ማድረጓን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉም 13 ሚሊዮን ሴቶችን ቀጥተኛ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያርግና በመጠቀም ላይ ላሉ 6 ሚሊዮን ሴቶች ጥቅም ላይ  እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ይፈሩ ብርሃን በበኩላቸው በቀጣዩ አመት በድጋፉ የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚ ለሚሆኑ ሴቶች ራሳቸው በክርናቸው ላይ የሚያደርጉት  አዲስ አይነት የእርግዘና መከላከያ ተግባር ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡

አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በማስተዋወቅ ጭምር አስፈላጊውን ተግባር እንደሚወጣ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ሪፖርተር ፡‑ ነፃነት ወርቁ