የኢጋድ አባል አገራት የብዝሀ ህይወት ፖሊሲ አጸደቁ

ሐምሌ 7፣2009

የኢጋድ አባል አገራት ብዝሀ ህይወትን በቅንጅት በማስተዳደር ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ የብዝሀ ህይወት ፖሊሲ አጸደቁ።

የአፍሪካ ቀንድ አከባቢ በብዝሀ ህይወት የበለጸገና አብዛኛው የመሬት አካልም ለእርሻ ተስማሚ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ይሁንና ቀጠናው በበዝሀ ህይወት አስተዳደር እጦትና እጥረት ምክንያት በሚነሱ ግጭቶች ከሚናጡና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተጎዱ ካሉ የአለም አከባቢዎችም ዋነኛው ነው።

ብዝሀ ህይወትን በአግባቡ በማስተዳደር የቀጠናውን ህዝቦች ኑሮ ማሻሻል ላይ ያተኮረው የኢጋድ አገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት በበዝሀ ህይወት ላይ የተጋረጠውን አደጋ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክሯል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አባል አገራት ብዝሀ ህይወትን በተቀናጀ ሁኔታ በማስተዳደር ዘላቂ  ልማት በማምጣት ህዝቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተስማምተዋል።

የሚንስትሮች ምክር ቤቱ የጋራ የሆነ የብዝሀ ህይወት ፖሊሲና ፕሮተኮልም ጸድቋል።

በጉባኤው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተጎዱ ታዳጊ አገራትን ለመደጎም የበለጸጉ አገራት የገቡትን ቃል እንዲተገብሩ ጥሪ ቀርቧል።

የኢጋድ አባል አገራት ፖሊሲውን የብሔራዊ  እቅዳቸው አካል በማድረግ ለተግባራዊነቱ  በቁርጠኝነት ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ሪፖርተር:-አለማየሁ ታደለ