ፓርቲዎች በመደራደሪያ አጀንዳዎች ቅደም ተከተል ላይ ተስማሙ

ሐምሌ 07፤2009

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር መድረክ ለሚያካሂደው ድርድር የተመረጡ አጀንዳዎችን ቅድመ ተከተላቸው ላይ ተወያይቶ አፀደቀ፡፡

ከሳምንት በፊት ፓርቲዎቹ ባፀደቋቸው 12 አጀንዳዎች የመደራደሪያ ቅደመ ተከተል መርሀ ግብር አዘጋጅተዋል፡፡

ለድርድር ከተመረጡት አጀንዳዎች መካከል የምርጫ ሕግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነ ምግባር አዋጅ ለመጀመሪያ መደራደሪያነት ተመርጠዋል።

በድርድሩ መጨረሻም ብሔራዊ መግባባት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ይወያይሉ ተብሏል፡፡

ፓርቲዎቹ መደራደር በፈለጉት ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን የሚገልፁት መጀመሪያ በጽሑፍ እንደሆነ መግባባት ላይ ሲደርሱ በሳምንት ሶስት ጊዜ ለመገናኘትም ተስማምተዋል፡፡

ድርድሩን በ9ዐ ቀናት ማዕቀፍ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታሳቢ ያደረገ የግዜ ሰሌዳ ይዘጋጃል ተብሏል፡፡

ሪፖርተር፦ሙባረክ መሐመድ