ኢህአዴግ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዲያ ፎረምን በፕሬዝዳንትነት እንዲመራ ተመረጠ

ሐምሌ 07፤2009

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር/ኢህአዴግ/ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዲያ ፎረምን በፕሬዝዳንትነት እንዲመራ ተመረጠ፡፡

ፓርቲው የተመረጠው ምክር ቤቱ በኒጀር ኒማይ ባደረገው ጉባኤ ነው፡፡

በጉባኤው የቻዱ የአርበኞች ንቅናቄ የናይጄሪያው ዲሞክራሲና ሶሻሊዝም ፓርቲ በምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡

የሚዲያ ፎረሙ አፍሪካን በአግባቡ በማስተዋወቅ በአህጉሪቱ ላይ ያሉ አሉታዊ አስተያየቶችን መቀየር ዋነኛ ዓላማው ነው ተብሏል፡፡

ፎረሙ በአፍሪካ የጋዜጠኝነት ሙያ እንዲያድግ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት የሀሳብ ብዝሀነትን ለማስተናገድ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ከ35 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 47 ፓርቲዎች የፎረሙ አባል መሆናቸውን የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ያደረሰንመረጃ ያመለክታል።