የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤውን ጀምሯል

ሐምሌ 07፣2009

የአማራ ክልል ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን  ድርጅት አስታወቀ፡፡

በጉባኤው መክፈቻ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ ምክር ቤቶች በውስጣቸው ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን ሁለንተናዊ በሆነ መልክ ተግባራዊ የሚደረግባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

በህብረተሰቡ ውስጥ የዴሞክራሲ አስተሳሰብ እንዲጎለብትና ስር እንዲሰድ በማድረግ ረገድም ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በጉባኤው የአስፈጻሚ አካላት የተጠቃለለ ሪፖርት ያያል፤የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ይቀርባል፤የዋና ኦዲተር ሪፖርትም ያደምጣል፤ በመጨረሻም የክልሉ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አፈጻጸምን ይመለከታል፡፡ ረቂቅ አዋጆችና ሹመቶችም ቀርበው ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ የጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ የጨፌ ስራ ዘመን 2ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ይጀምራል፡፡

ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው ለመጪዎቹ  ሶስት ቀናት ነው፡፡

በስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ውይይት እንደሚደረግባቸው የጨፌ ኦሮሚያ ፅሕፈት ቤት ሀላፊ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡