ኦንቴክስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዳይፐር ማምረቻ ፋብሪካ ከፈተ

ሐምሌ 6፤2009

ኦንቴክስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የካንቤቤ ዳይፐር ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ በይፋ ከፈተ᎓᎓

ዛሬ የተከፈተው ፋብሪካ ኦንቴክስ ለአፍረካውያን ቤተሰቦች የሚያስፈልገውን የህጻናት ዳይፐር ፍላጎትን ለማሟላት ይረዳል ነው የተባለው፡፡

ኦንቴክስ የግል ንጽህና መጠበቂያዎችን ከሚያመርቱ አለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል በኢትዮጵያ የማምረቻ ፋብሪካ ሲከፍት የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡

ይህ ፋብሪካ የኦንቴክስ የማስፋፊያ እስትራቴጂ አንዱ አካል ሲሆን  ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ባሉ ሀገራት ውስጥ ምርቶቹን በማቅረብ ተወዳዳሪ ለመሆን እቅድ ይዞ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው ᎓᎓

የኩባኒያው የገበያ ዲቪዥን ዋና ሃላፊ ቴሪ ቪያል እንደገለጹት ከሆነ ይህ የተከፈተው የማምረቻ ፋብረካ የምስራቅ አፍሪካ ተጠቃሚዎችንጅ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ከአካባቢው ሰራተኞችን መልምሎ በማሰልጠን ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢዝነስ ኢንሳይደር