የኔዘርላንድስ ተመራማሪዎች በባህር ላይ ተሳፋፊ ከተማ እውን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ሞዴል ይፋ አደረጉ

ሐምሌ 05፣2009

የኔዘርላንድስ ተመራማሪዎች በባህር ላይ ተሳፋፊ ከተማ እውን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ሞዴል ይፋ አደረጉ፡፡

የቦታ እጥረትን ችግር ለመቅረፍና ለልዩ አገልግሎት ተመራማሪቹ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት አመታት እውን ሊሆኑ የሚችሉ ተንሳፋፊ ደሴት ከተሞችን  ሞዴል ነው ትላንት ይፋ ያደረጉት፡፡

የተንሳሳፊ ከተሞቹ  ንድፍ  ቤቶችን፣ወደቦችን፣ የእርሻ መሬቶችንና  ፓርኮችን  የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡

ተመራማሪዎቹ ለሙከራ ይፋ ያደረጉት  የተንሳፋፊ ከተማ ሞዴል ከብረትና ሲሚንቶ ልስን የሚሰሩ 87 የሚደርሱ የተለያዩ የሶስትዮሽ ቅርፅ ያላቸው ግንባታዎችን የያዙ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ተንሳፋፊ ከተማ እስከ ሶስት ኪሎ ሜትር ስኩዌር ስፋት ይኖረዋል በንድፉ መሰረት፡፡

ከኔዘርላንድስ የባህር ላይ ምርምር ተቋም  ኦላፍ  ዋላስ እንደሚሉት የኔዘርላንድ ከተሞች እንደመዝናኛና ሌሎች ተግባራት ላይ እውን ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል፡፡

የተንሳፋፊ ደሴቶች እቅድ እውን የሚሆን ከሆነ ለኔዘርላንድስ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል፡፡

ትላንት ይፋ የተደረገው ባለ 48 ስኩዌር ካሬ የተንሳፋፊ ከተማው ሞዴል  የባሃብቶችን ቀልብ ለመሳብና ለሙከራ ተመራማሪዎቹ በግዙፍ የውሃ ገንዳ ላይ አስቀምጠው ለእይታ ክፍት አድርገዋል፡፡ ይሁንእንጂ አሁን ይፋ የተደረገው ይኸው ፕሮጀክት  ገና ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩት ግን ተመልክቷል፡፡እቅዱን እውን ለማድረግ ከ10 እስከ 20 አመት እንደሚፈጅ ግን ተገምቷል፡፡

ምንጭ፡‑ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ