የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

ሐምሌ 04፤2009

ወጣቶች በክረምት ወቅት በሚሳተፉባቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ ህብረተሰቡን በንቃት እንዲያገለግሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

ወጣቶቹም ለህብረተሰቡ የሚሰጡት የበጎ አገልግሎት ተግባር መነቃቃትን እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡

የ2009 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ የአገልግሎት የከባቢ ልማት፤ ጤናና ሰብዓዊ አገልግሎቶችን ጨምሮአምስት የተለያዩ ዘርፎች ያካተተ ሲሆን 900 መቶ ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡

15ኛው የአዲስ አበባ ከተማና 4ኛው የፌደራል የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀምሯል፡፡

በሜሮን በረዳ