የቱርክ አውቶሞቲቭ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ ነው

ሐምሌ 04፤2009

ኢትዮጵያና ቱርክ ጠንካራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነት በመፍጠራቸው የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚፈልጉ የቱርክ አውቶሞቲቭ ኩባኒያዎች ገለጹ፡፡

የቱርክ የአውቶሞቲቭ ድርጅቶች ልኡካን ዛሬ በአዲስ አበባ የቢዝነስ ዝግጅት በተካሄደበት ወቅት አንዳንድ የኢትዮጵያ የቢዝነስ ተሳታፊዎች እንደገለጹት በዝግጅቱ ከቱርክ ልኡካን ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ችለዋል፡፡

የቱርክ አውቶሞቶቭ ድርጅቶች ልኡካን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በኢንደስትሪው ዘርፍ ሰፊ እድል እንዳላትና በኢትዮጵያም በአውቶሞቲቭ ኢንቨስትመንት ዘርፉ መሳተፍ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

በቢዝነስ ዝግጅቱ ላይ የተሳተፈው የቱርክ የንግድ ልኡካን መካከል የመኪና እቃ መለዋወጫ እንዲሁም የተሽከርካሪና አውቶሞቲቭ ዘይቶች አቅራቢ ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፡ ኢቢሲ