ቻይና በጅቡቲ ወደ መሰረተችው የጦር ሰፈር ወታደሮቿን አንቀሳቀሰች

ሐምሌ 04፣2009

ቻይና በጅቡቲ ወደ መሰረተችው የጦር ሰፈር ወታደሮቻን አንቀሳቀሰች፡፡

በጅቡቲ የሚሰፍረውን ጦር የያዘችው የቻይና የጦር መርከብ በዛሬው ዕለት ወደ ስራፍራው አንቀሳቅሳለች፡፡

የአገሪቱ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሸን ጂንሎንግ በጅቡቲ ለሚሰፍረው የባህር ኃይል መመሪያ ሰጥተው ሸኝተዋል፡፡

በጅቡቲ የተመሰረተው የቻይና የጦር ሰፈር  በሁለቱ አገራት ስምምነትና የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን የባህር ኃይሉ ዋና አዛዥ ለሽንዋ ገልፀዋል፡፡

በጅቡቲ በተቋቋመው የቻይና የጦር ሰፈር  የሚሰማራው ጦር በአፍሪካና በምዕራብ ኢስያ እንደ ሰላም ማስጠበቅና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተልዕኮዋን ለመከወን እንደምትገለገልበት ቻይና አስታውቃለች፡፡

በተጨማሪም ከቻይና ውጭ ለሚካሄዱ ወታራዊ የጋራ ልምምዶች፣ ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና ለነፍስ አድን ተልዕኮ ወታደራዊ ሰፈሩ ሁነኛ መገልገያ እንደሚሆንም የሽንዋ ዘገባ ያመለክታል፡፡