የኢትዮጵያና ጂቡቲ የውሃ ፕሮጀክት በቅርቡ ይጠናቀቃል

ሃምሌ 4፤2009

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ድንበር ተሸጋሪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ ከሰባት መቶ ሺህ በላይ  የጂቡቲ ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 በአፍሪካ ትልቁ የውሃ ፕሮጀክት መሆኑ የተገለፀው  የኢትዮ- ጂቡቲ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከቻይና በተገኘ ገንዘብ ድጋፍ እተከናወነ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የፕሮጀክቱ  ሂደት ከሶስት ሳምንታት በፊት ሙከራ ስራ ተከናውኖ ጥሩ ውጤት ማሳየቱን የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ደመላሽ ሙሉ ተናግረዋል፡፡

በ329 ሚሊዮን ዶላር በሃምሌ ወር 2007 ግንባታው የተጀመረው የኢትዮ-ጂቡቲ የውሃ ፕሮጀክት   የጂቡቲን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት  የታቀደ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካን ሪቪው