በየመን አስከፊ የኮሌራ በሽታ መቀስቀሱ ተነገረ

ሰኔ 18፤2009

በየመን እጅግ አስከፊ የሆነ የኮሌራ  ወረርሽኝ  መቀስቀሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በየመን የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ  እስከ ዛሬ  በአለም ላይ በየትኛውም በየትኛውም አከባቢ ተከስቶ  እንደማይታወቅ  በመግለጽ  አስጠንቅቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ እና የአለም ጤና ድርጅት እንደገለጹት በየመን በኮሌራ በሽታ የተያዙ  ሰዎች ቁጥር 200ሺህ  ደርሷል፡፡

በበሽታው ከተያዙት መካከል 1ሺህ 300ዎቹ የሞቱ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል 1/4ኛ የሚሆኑት ህፃናት ናቸው ተብሏል።

 የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ድርጅቱ  ገልጿል፡፡

ሁለቱ የመንግስታቱ ድርጅቶች የበሽታውን ስርጭት ለማስቆም የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል፡፡

የበሽታው ስርጭት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በአብዛኛውን የአገሪቱ ክፍል መዳረሱንና   በቀጣይም  በየቀኑ 5ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታ ሊያዙ ይችላሉ የሚል ግምት መኖሩ  ተገልጿል፡፡

ሆስፒታሎች በበሽታው በተያዙ ሰዎች መጨናነቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡