የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለልብ ህክምና ዘመናዊ መሳሪያዎችን መጠቀም ጀመረ

ሰኔ 16፤2009

በአገሪቱ የልብ ህክምና ቁሳቁስም ሆነ ክህሎቱ ባለማደጉ ብዙዎች ህክምናቸውን ሳያገኙ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነግሯል፡፡

አብዛኞቹ ታካሚዎች ወደ ውጪ ሀገር ሄደው እንዲታከሙ ቢወሰንም የኢኮኖሚ ችግር ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደነበር ተገልጿል፡፡

እነዚህን አሳሳቢ ችግሮች ለመቀነስ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምናው ቴክኖሎጂ የደረሰበት ነው የተባለ የህክምና መሳሪያ በመጠቀም ለህሙማኑ አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል᎓᎓

ዘመናዊው ህክምና ለሚሰጥበት  ለመሳሪያዎቹ ግዥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ላይ ወጪ መደረጉን ነው ሆስፒታሉ የገለጸው᎓᎓

ከስዊድንና ኖርዌይ በመጡ ባለሙያዎች በተሰጠ ስልጠናና ትብብር በ15 ቀናት ውስጥ 64 ታካሚዎች

ህክምናውን አግኝተዋል᎓᎓

በዳዊት ጣሰው