ኢትዮጵያና ኩዌት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ሰኔ 12፤2009

የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ከኩዌት አቻቸው ሼክ ሰባህ አልካሊድ አልሻባህ ጋር በኩዌት ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ሚንስትሮች የአገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች እና በቀጠናው ባለው ውጥረት ላይ ስላላቸው የጋራ አቋም ነው የተነጋገሩት፡፡

የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለኩዌት አሚር ሼክ ሰባህ አል አህመድ አልጃቢር የተላከውን ደብዳቤ ሰጥተዋቸዋል፡፡

የደብዳቤው ይዘት የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም የቀጠናውንና ዓለማቀፍ ጉዳዮችን የተመለከተ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በባህረ ሰላጠው አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት የኩዌቱ አሚር ሼክ ሰባህ አል አህመድ አልጃቢር ላደረጉ ብስለት የተሞላበት ጥረት አድናቆታቸውን  በደብዳቤው አካተዋል፡፡   

ምንጭ፡- kuna.net.kw