የረጲ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ በመጪው መስከረም ስራ ይጀምራል

ሰኔ 12፤2009

ከቆሻሻ ሃይል የሚያመነጨው ፕሮጀክት በመጪው መስከረም ሃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ይህ የሃይል ምንጭም በፍጥነት እያደገ ለሚገኘው የአገሪቱ  ኢኮኖሚ የራሱን ድርሻ እንደሚያበረክት ነው የተገለፀው᎓᎓

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ረጲ አካባቢ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በመጪው መስከረም ወር ሃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነትን የሚያጠናክርና ኢትዮጵያ ለጀመረችው የአረንጓዴ ሃይል ግንባታ አንድ ማሳያ እንደሆነ ነው የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ዋና ሃላፊ ወይዘሮ አዜብ አስናቀ የተናገሩት᎓᎓

የሃይል ማመንጫው በቀን 1 ሺህ 280 ቶን ቆሻሻን በማቃጠል ይጠቀማል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት 100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በመመደብ የቻይናው ናሽናል ኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ግንበታውን እያከናወነ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ግሎባል ታይምስ