የአፍሪካ ሕብረት ኤርትራና ጂቡቲ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት እንዲያረግቡ ጥሪ አቀረበ

ሰኔ 11፤2009

የአፍሪካ ሕብረት ኤርትራና ጂቡቲ  በመካከላቸው  የተፈጠረውን ውጥረት  እንዲያረግቡ ጥሪ አቀረበ።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂ ማሃማት  በሁለቱ አገራት መካከል በዱሜሪያ  ደሴት ዙሪያ  የተከሰተውን ውጥረት ለማርገብ ኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ወደ አገራቱ ድንበር አከባቢ እንደሚልክ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሕብረት በአገራቱ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንደሚሰራና አገራቱም ውጥረትን ከሚያባብሱ ተግባራት ሊቆጠቡ እንደሚገባ ኮሚሽነር ሙሳ ፈቂ ጥሪ አስገንዝበዋል።

ታር ከዱሜሪያ ደሴት ላይ ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ባለፈው ዓርብ ኤርትራ  በደሴቷ ላይ ወታደሮቿን በማስፈሯ ጅቡቲ ኤርትራ መልሳ ግዛቴን ወረረች ስትል መክሰሷ ይታወሳል።

 አገሪቱ ሊሰነዘርባት የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ጦሯን ዝግጁ ማድረ ማስታወን ተከተሎ ነው በሁለቱ አገራት መካከል ውጥረት የተፈጠረው።

የጅቡቲ  የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሀሙድ አሊ የሱፍ ባለፈው ዓርብ ከኤርትራ ጋር የሚዋሰኑባቸውንና ሲወዛገቡባቸው የቆዩት የዱሜራ ተራራንና ደሴት ኤርትራ መልሳ መውረሯ መናገራቸው ይታወሳል።

ምንጭ:-አልጀዚራ