ተመድ የሶማሊያ ተልዕኮውን አራዘመ

ሰኔ 10፤2009

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ ያለውን ተልዕኮ እስከ ፈረንጆቹ ሚያዝያ 2018 እንዲራዘም በአብላጫ ድምጽ መወሰኑ ተገልጸ፡፡

ምክር ቤቱ ተልዕኮውን ለማራዘም የወሰነበት ምክንያት በሀገሪቱ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ የሰብዓዊ ቀውስ የሚያመጣውን ጫና ለመቋቋምና የፖለቲካ ሂደቱ ወደ ተፈለገው ደረጃ እንዲደርስ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም የእርዳታ ድርጅቶች ለሀገሪቱ ተጎጂ ዜጎች የሚያደርሱትን አስቸኳይ እርዳታ ማዳረስን የሚያደናቅፍ ማናቸውንም አካል የሚቃወም ሲሆን ለአላማው ስኬት ሁሉም እንዲተባበር ጠይቋል፡፡

 የሀገሪቱ ፌደራል መንግስትም  ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውህደትን እንዲፈጥር ቁርጠኛ መሆን እንዳለበትና ምክርቤቱም አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ተመድ