አርኪዮሎጂስቶች በምስራቅ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተማ አገኙ

ሰኔ9፤2009

በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ሃርላ በተባለ አከባቢ ጥንታዊ ከተማ በቁፋሮ ማግኘታቸውን አርኪዮሎጂስቶች አስታወቁ።

በከተማዋ የግብጽ፣ የህንድና የቻይና የተለያዩ የእደጥበብ ውጤቶች መገኘቱን ተመልክቷል፡፡

በ12ኛ ክፍለ ዘመን የተገነባ በታንዛኒያና በሶማሌላንድ ካሉ የሚመሳሰል መስጊድ  መገኘቱንም ተገልጿል፡፡   

ይህም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በሚኖሩ የእስልምና ማህበረሰቦች መካከል ታሪካዊ ግንኙነት መኖሩን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

አዲሱ የአርኪዮሎጂ ግኝት ጥንታዊ ከተማዋ ከውጪ ሀገሮች ጋር የንግድ ትስስር እንደነበራት ግንዛቤ የሚፈጥር ነው ብለዋል የአርኪዎሎጂ ምርምሩ ዋና መሪ ፕሮፌሰር ቲሞዚ ኢንሶል፡፡ 

በጥንታዊ ከተማዋም የማዳጋስካር፣ የመን፣ የማልዲቭስና የቻይና የጌጣ ጌጥና ሌሎች የእደጥበብ ውጤቶች መገኘቱ ተገልጿል፡፡

የምርምር ቡድኑ እንዳለው በወቅቱ ባሉ ነዋሪዎች ላይ ተጨምሪ ምርምር ለማድረግ በከተማዋ ባሉ መካነ መቃብር በጥቂቱ በ300 የሰዎች አጽሞች ላይ ጥናት ይካሄዳል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ