የጃፓን የንግድ ተቋማት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

ሰኔ7፤2009

በጃፓን የሚገኙ የተለያዩ የንግድ ተቋማት በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጃፓን የሚገኙ  የኢንቨስትመንት ልኡካን ቡድኖችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የጃፓን የውጪ ንግድ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሱሚ ሄራኖ እንደገለጹት ጃፓን በኢትዮጵያ እንደ ጨርቃ ጨርቅ፣ ጤና ግንባታ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ጉብኝቱም ወደ ኢቨስትመንት ዘርፉ ለመቀላቀል ለሚያደርጉት ጥናት አንዱ አካል መሆኑንም ተናግረዋል።

በጃፓን ያሉ ሌሎች ባለሀብቶችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በቃል አቀባያቸው እንደገለጹት በጃፓን የሚገኙና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ሰላሳ ሁለት የንግድ ተቋማት ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመው ጃፓን በኢትዮጵያ ለምታደርገው ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ ሙሉ ድጋፍ ታደርጋለች።

ሪፖርተር:-ሜሮን በረዳ