አየር መንገዱ አሪክ ኤይርን ለማስተዳደር እየተወያየ ነው

ሰኔ 2-2009

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጄሪያ የንብረት አስተዳደር ኮርፖሬሽን  በበላይነት ሲመራ የነበረውን አሪክ አየር መንገድን አስተዳደራዊ ስራውን ለመረከብ ከናይጄሪያ መንግስት ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ እና የናይጄሪያ ፌደራል መንግስት በአቡጃና አዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ሶስት ጊዜ በመገናኘት በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረተጋቸው ተነግሯል፡፡

የአስተዳደራዊው ስራ ስምምነቱ ዋና አላማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሪክ አየር መንገድን አስተዳደራዊ ስልጣንን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብና ቴክኒካላዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ ዚስዴይ ላይቭ