ቀዝቃዛ ውኃ የሞቀ ውኃን ያህል ቆሻሻ የማስለቀቅ አቅም አለው:- ጥናት

ግንቦት 27፣2009

እጅን ለመታጠብ ቀዝቃዛ ውኃ የሞቀ ውሃን ያህል ቆሻሻ የማስለቀቅ አቅም እንዳለው አንድ ጥናት አመለከተ።

በሀያ ሰዎች ላይ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው 15 ዲግሪ ሴንት ግሬድ ሙቀት ያለውና    18 ዲግሪ ሴንት ግሬድ ሙቀት ያለው ውሀ እኩል የማጽዳት አቅም አላቸው።

ብሔራዊ የጤና  አገልግሎት በቀዝቃዛም ይሁን በሞቀ ውኃ እጅን መታጠብ አስፈላጊ እንደሆነ ይመክራል።

የሩትገርስ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶችም እጅን በቀዝቃዛ ውኃ ከመታጠብ ይልቅ በሞቀ ውኃ መታጠብ ብዙ ጀርሞችን ይገድላል የሚለውን አስተሳሰብ ለመለየት ጥናቱ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።

በዚህም እጅን በሞቀም ሆነ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ እንዲሁም ማንኛውንም አይነት ሳሙና መጠቀም አንድ አይነት ውጤት እንዳለው አረጋግጠናል ብለዋል።

ሰዎች እጃቸውን ሲታጠቡ ምቾት ተሰምቷቸው ሊታጠቡ ይጋባል፥ ዋናው ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው የአስተጣጠብ መርሆቹ ላይ እንጂ የውኃው ሙቀት ወይም ቀዝቃዜ ላይ አይደለም ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው እጅን ቢያንስ ለሀያ ሰከንድ በደንብ በማሸት መታጠብ አስፈላጊ ነው።

እጅን በመታጠብ ብቻ ውኃ ወለድ፣ የአይን፣ የጉበትና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል እንደሚቻል መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ:- ቢቢሲ