የአልኮል መጠጥ የካንሰር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል፦ ተመራማሪዎች

ግንቦት 22፤2009

በየቀኑ የአልኮል መጠጥን መውሰድ ሴቶች ለጡት ካንሰር በሽታ የመጋለጥ እድላቸውን እንደሚጨምር አንድ ጥናት አረጋገጠ፡፡ 

የዘርፉ ተመራማሪዎች ከዚህ ቀደም የተደረጉ 119 ተመሳሳይ ጥናቶችን በመከለስ 12 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት ነው ይህን አዲሱን ግኝት ይፋ ያደረጉት ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት በቀን አንድ አነስተኛ ብርጭቆ ወይን ወይም ቢራ አልያም ጠንካራ የአልኮል መጠጥ መጎንጨት የሴቶችን የካንሰር በሽታ ተጋላጭነት ይጨምረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ ሩጫና ፈጣን የቢስክሌት ግልቢያ የመሰሉ ጠንካራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸውን በ17 በመቶ እንደሚቀንስ ተነግሯል፡፡

ጥናቱ የአሜሪካ የካንሰር ምርምር ተቋምና የአለም የካንሰር ምርምር ፈንድ ምርምር ውጤት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ምንጭ፦ዴይሊ ሜል፣ ሳይንስ ዴይሊና ሲቢኤስ ኒውስ