የውቅያኖስ ጠለል የመጨመር ፍጥነት በሶስት ዕጥፍ አድጓል

ግንቦት 16- 2009

ውቅያኖሶች በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩበት የመጨመር ፍጥነታቸው በሶስት እጥፍ ገደማ ማደጉን ሳይንትስቶች ገልጸዋል፡፡

በጀርመን፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይና በኔዘርላንድ ተቋማት ተመራማሪዎች የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው የባህር ጠለሉ ከቀድሞ ይልቅ በአሁን ሰአት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ጥናቱ እንዳመለከተው ከ1990 በፊት የነበረው የባህር ጠለል በአመት 1.1  ሚሊ ሊትር አከባቢ ነበር ይጨምር የነበረው፡፡

ነገር ግን እአአ ከ1993 እስከ 2012 ድረስ የባህር ጠላል በየአመቱ 3.1 ሚሊ ሊትር መጨመሩን የዘ ኢንድፔንዳንት ዘገባ ያስረዳል፡፡