ለናይጀሪያ ድርቅ ቦኮሃራም ሌላኛው እንቅፋት መሆኑን ተመድ ገለፀ

ግንቦት 11፣2009

በናይጅሪያ ለድርቅ ለተጋለጡ ዜጎች የሚደረገውን እርዳታ ቦኮሃራም የተባለው አሸባሪ ቡድን እያደናቀፈ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

እንደ ድርጅቱ ዘገባ በናይጀሪያ በተከሰተው ድርቅ እስከ 1.8 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ ይሻሉ፡፡

ይሁን እንጅ የቻድ እና ኒጀር አዋሳኝ ድንበሮች በቦኮሃራም ቁጥጥር ስር የሚገኙ በመሆኑ ድጋፉን ለመስጠት አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል፡፡

በበኮሃራም ቀጠና እስከ 6 መቶ ሺህ የሚደርሱ ከድርቅ ጋር የሚኖሩ ናይጀሪያውያን ይገኛሉ ይላል ዘገባው፡፡ ነገር ግን በቡድኑ ምክንያት ለእነዚህ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አልተቻለም፡፡

በተለይ የናጅጀሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍል ስደተኞች የሚበዙበት በመሆኑ ህፃናት የከፋ ጉዳት እያስተናገዱ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ለናይጀሪያ ድርቅ ተጎጅዎች 230 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን