አሜሪካ ለውጭ አገራት የጤና ፕሮጀክቶች ይውል የነበረን የ9 ቢሊዮን ዶላር በጀት ልትቀንስ ነው

ግንቦት 11 ፣2009

አሜሪካ ለውጭ አገራት የጤና ፕሮጀክቶች ይውል የነበረን የ9 ቢሊዮን ዶላር በጀት ልትቀንስ  መሆኑን አስታወቀች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔውን  ያሳለፉት ቀደም ብለው በፈረሙት ፕሬዝዳንታዊ ማስፈፀሚያ ሰነድ በውጭ አገራት ስነ ተዋልዶ ላይ በተለይም  በተፈቀደ ውርጃ ላይ  ትኩረት አድርገው የሚሰሩ የአሜሪካ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በጀት የሚገድብ ነው፡፡

በዋነኛነት በአሜሪካ የሰነ ተዋልዶ ጤና ድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑ የአፍሪካ አገራትን የሚጎዳ ውሳኔ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

አሜሪካ አሁን በምትወስደው እርምጃ አፍሪካ ለኤች አይቪ ኤድስ መርሃ  ግብር  አገልግሎት ታገኝ የነበረውን  የ6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ  የሚያሳጣት ይሆናል  ተብሏል፡፡

ይሁንጂ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሳለፉት ውሳኔ ወደ ተግባር ለማግባት ወራት ይፈጅበታል ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም አሜሪካ ለውጭ አገራት ከምትሰጠው የጤና ድጋፍ ቅነሳ ስታደርግ ከ6 ማቶ ሚሊዮን ዶላር በልጦ እንደማያውቅና የአሁኑ የ9 ቢሊዮን ዶላር ቅነሳ የተጋነነ በመሆኑ  በአገሪቱ ታሪክ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ምንጭ፡‑ ሲቲጂኤን