አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በአቨዬሽን ስጋት ላይ ለመወያየት በዋሽንግተን ሊሰባሰቡ ነው

ግንቦት 10፣ 2009

አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በአቨዬሽን ስጋት ላይ ውይይት ለማድረግ በሚቀጥለው ሳምንት  በዋሽንግተን   እንደሚሰበሰቡ ተገለጸ፡፡

የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣነት በሚቀጥለው ሳምንት በዋሽንግተን የሚሰበሰቡት በአየር ጉዞ ላይ የተጋረጠውን አደጋ በተመለከተ በቤልጂየም ብራሰልስ  ከተሰበሰቡ በኋላ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ውይይት ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁለቱም  ወገኖች ብራሰልስ  ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ለአቨዬሽን ደህንነት ትልቅ ስጋት በሆኑ ጉዳዮች ላይ መረጃ መመለዋወጣቸውና ስጋቱን መጋፈጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደህንነት ቃል አቀባይ በአየር ጉዞ ላይ የሚከለከሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ የተሰጠ ውሳኔ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፤ ሮይተርስ