የኦሮሚያ የዲያስፖራ ዜጎች በተሰጠው ጊዜ ገደብ እንዲመለሱ እየሰራ ነው

ግንቦት 10፣ 2009

የኦሮሚያ የዲያስፖራ ኮሚቴ ከሳውዲ ያሉ ዜጎች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ  በአካባቢው ካሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎቸን  እየሰራ ይገኛል᎓᎓

ተመላሽ ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው ለመለወጥ ፍላጎትና ዝግጅት ካላቸውም በሃገሪቱ የተለያዩ የስራ አማራጮች መኖራቸው ነወ የተገለፀው᎓᎓

በተሰጠው የጊዜ ገደብ መመለስ ከእንግልትና ከእስር ለመዳን ከማገዙም በላይ ህጋዊ በሆነ አግባብ ወደ ሳውዲ መመለስ ለሚፈልጉ ዜጎች አማራጭ የሚሰጥ መሆኑንም ነው የቦርዱ ሰብሳቢ አቶአብዱል አዚዝ የገለፁት᎓᎓

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የገለፁት አቶ አብዱል አዚዝ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ኖሯቸው በሳውዲ የሚኖሩ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች በማነሳሳት በጊዜ እንዲመለሱ ማድረግ የዜግነት ግደታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡            

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሃገሪቱ የሚኖሩ የተለያዩ ሃገራትዜጎች ከሃገሩ እንዲወጡ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል᎓᎓

ኢትዮዽያም ከሳውዲ መንግስት የተሰጠው የጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊተ ዜጎቿ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ትገኛለች᎓᎓

ሪፖርተር፣ ተመስገን ሽፈራው