የአብዬ ግዛት የሰላም ማስከበር ቆይታ ለ6 ወራት ተራዘመ

ግንቦት 10፣ 2009

የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ለሰላም ማስከበር ተልዕኮው በአብዬ የተሰማራው ብቸኛው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ቆይታ ለ 6 ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ በያዝነው ወር ይጠናቀቅ የነበረው የሰላም አስከባሪ ሃይል ቆይታ ጊዜ እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ የቀረበው በኢትዮጵያ በኩል ሲሆን የምክር ቤቱ አባላትም ኢትዮጵያ ለአቢዬ ሰላም ያደረገችውን አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በተመድ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሰደር ዶ/ር ተቀዳ አለሙ እንዳሉት ኢትዮጵያ በምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል ሆና ከመመረጧ አስቀድሞ ለአብዬ ሰላም ከተለያዩ ምክር ቤት አባላት ጋር ስትሰራ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡

በአቢዬ የሰላም አስከበሪ ሃይል ያሰማራችው ኢትዮጵያ የጎረቤት ሃገራትን ሰላም በማስከበር የድርሻዋን እየተወጣች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ምንጭ፡ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር